ሀከሮች እንዴት ነው አካውንታችንን ሃክ የሚያደርጉት ? ክፍል 2



ቸልተኝነት

 በማወቅም ሆነ በመዘናጋት የምንፈጥራችው ክፍተቶች ለሃከሮች በቀላሉ ኢሜላችንን ወይንም ፌስቡካችንን ሃክ እንዲያደርጉ ያደርጋል፡፡ ለምሳሌ ኢንተርኔት ካፌ ውስጥ ተጥቅመን ስንጨርስ ሎግ አውት ሳናደርግ ብራውሰሩን ክሎዝ አድርገን እንወጣልን፤ ይህ ማለት ቀጥሎ የሚመጣው ሰው ብራውሰሩን መልሶ ሲከፍተው እኛ መጨረሻ ላይ ዘግተን የወጣነውን ገጽ ነው የሚከፍትለት ይህም ፌስቡክ ወይንም አሜይላችን ቀጥታ ከፈተለት ማለት ነው፡፡ 

አንዳንድ ጊዜ ደግሞ አካውንታችን ሎግ ኢን ስናደርግ ፓስዎርዳችንን ሴቭ ላድርግላቹ የሚል መልእክት ብቂ ሲል በቸልተኝነት ሳናነብ የስ እንለዋለን ይህም ማለት ዩሰር ኔማችን እና ፓስዎርዳችን ኮመፒውተሩ ላይ ሴቭ ተደረገ ማለት ነው በሌላ አገላለፅ ከ ቆይታ በኋላ በቀላሉ ፓስወርዳችንን ሶስተኛ ወገን ማግኘት ይችላል ማለት ነው፡፡

 ግምት 

ይህ መንገድ ብዙ ጊዜ በአቅራቢያችን በሚገኙ ለማጅ ሀከሮች የሚደረግ ነው፡፡ ይህም በቃላሉ ፓስዎርዳችንን በመገመት ኢሜላችንን ወይንም ፌስቡካችንን ሃክ እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል፡፡ ለምሳሌ በእኛ አገር የተለመደው ፓስዎርዳችንን ስልክ ቁጥር እናደርጋለን ብዙ ጊዜ ላለመርሳት አናዳዴም እንደዚው ስለመጣለን እናደርገዋልን ወይንም የምንወደውን ሰው ስም ወይንም ስልከ ቁጥራቸውን እናደርጋለን ይሄ ደገም በቀላሉ የሚገመት እና አጋለጭ ነው፡፡ 
የራስ ሰልክ ቁጥር፣ የፍቅረኛ ስልክ ቁጥር ወይንም ስም፤የእናት ስም የተለመዱ የሀገራችን ፓስዎረድ ናቸው፡፡

ማታለል 

ብዙም ባያጋጥምም አንዳንዴ ከማናውቃቸው ላኪዎች በኢሜላችን ፓስወረዳችንን እንጠየቃለን አሳማኝ ለማስመሰልም በተደራጀ መልኩ የተዘጋጀ ቅፅ እንዲሁም ኢሜይሉ ከታማኝ ምንጭ ወይም ከታዋቂ ድርጅት እንደተላከ እና ፎረሙን በመሙላታችን ወይንም መልስ በመፃፉ ተጠቃሚ እንደምንሆን አድርገው ሊያታልሉን ይችላሉ፡፡ እንዲዚህ አይነት መልእክቶች ሲመጡ በጭራሽ መመለስ የለብንም፡፡አንዳዴ ፓስዎረዳችንን ብቻ ሳይሆን በተጨማሪም የባንክ አካውንት ቁጥር ጭምር ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ 

ፒሺንግ 

ይሄኛው መንገድ የፕሮገራሚንግ እውቀት የሚጠይቅ ሲሆን የተፈለገውን አካውንት ሃክ ለማድረግ ተመሳሰይ የሆነ ገፅ በመገንባት ዩሰር ኔም እና ፓሰዎረዳችንን ለሶስተኛ ወገን የሚተላለፍበት መንገድ ነው፡፡ ለምሳሌ ፌስቡክን ሃክ ማድረግ ከተፈለገ ከፌስቡክ ጋር በጣም ተቀራራቢ የሆነ ካልተጠነቀቅን በጣም ተመሳሳይ የሆነ ዌብሳይት በመስራት እኛ ፌስቡክ መስሎን ኢሜልን አና ፓስዎረድ ስናስገባ የኛነን መረጃ ወደ ትክክለኛው ፌስቡክ እንደ መላክ ወደ ሀከሮቹ መረጃችንን ይለካል ማለት ነው፡፡ ፒሺንግን ለመከላከል ዋንኛው መንገድ የምንጎበኘውን ዌብሳይት እራስችን በቀቀጥታ በመጻፍ መከላከል አነችላለን፡፡ ለምሳሌ www.facabook.com ወይንም www.facbooc.com ወይንም ደግሞ አድራሻው ከፌስቡክ ጋር የማይገናኝም ሊሆን ይችላል www.newbook.nt78.net ሊሆን ይችላል፡፡ ምንጊዜም እኛ የምንፈልገው ፌስቡክ እነዳልሆነ ኢሜላችንን ከማስገባችን በፊት መገንዘብ ይኖርብናል፡፡ አንዳንዴ ደግሞ ፋጽሞ የማይገናኝ አድራሻ ወይንም ቀጥር (አይ ፒ አድሬስ) ሊሆን ይችላል ገፅታው ግን እኛ ከምናውቀው ፌስቡከ ወይንም ያሆ ጋረ ፈፅሞ ተመሳሳይ ሊሆን ሰለሚችል ምንጊዜም አድራሻውን መገንዘብ ይኖርብናል፡፡ 

ጥንቃቄዎች

  • በተቻለን መጠነ ፓሰወረዳችን ረዘም ማድረግ 
  • በቀላሉ የማይገመቱ ፐሰዎረዶችን መጠቀም
  • የኛ ባልሆነ ኮመፒውተር ስንጠቀም ብራውሰሩ ፓስዋርዳችንን ላስታው (Remember your password) በሎ ሲጠይቀን ምንጊዜም ክሎስ ማድረግ ወይንም No ማለት ይኖርብናል፤ በርግጥ አንደ ምንጠቀመው ብራውሰረ የሚጠይቀን ጥያቄ ሊለያይ ይችላል ሆኖም ቁምነገሩ ፓስዎረዳችንን የኛ ያልሆነ ኮመፒውተር ሴቭ እንዲያደርገው አንፍቀድለት፡፡ 
  •  በከፍተኛ ባለሙያዎች የሚደረጉ ሃኪንጎችን ለመከላከል ፓስዎረዳችንን የተለያያ ካራክተሮች ቀላቅለን መጠቀም፡፡ ለምሳሌ ቁጠር እና ፊደልን አንድላይ መጠቀም በተጨማሪም ኪይቦርዳችን ላይ የሚገኙ ምልክቶችን መጠቀም ይቻላል 
  •  ኢነተርኔት ካፌ ውስጥ ስንጠቀም ሎግ አውት ማድረጋችንን እርገጠኛ ሆነን መውጣት 
  •  የራስችን ኮመፒወትር ከሆነ ደግሞ በዩሰር አካውንት መቆለፍ ፡፡ ሂንት መስጠት ካለበን ደግሞ የምንሰጠው ሂንት ቀጥታ ፐስዎረዱን ሳይሆን ፓስዎረዳችንን ሊያስታውሰን የሚችል ብቻ ነው መሆን ያለበት፡፡ 
  •  በተጨማሪም ምንጊዜም አንቲቫይረሳችንን በተቻለ መጠን አፕዴት ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡

0 comments:

Post a Comment

ShareThis