የኮምፒውተር ቨይረስ /Malware/ ምንድነው ? ክፍል ሁለት


ቫይረስ /Virus/ 

የኮምፒውተር ቫይረስ እራሱን ሌሎች ፋይሎች ላይ በማጣበቅ የሚያባዛ እና ተላላፊ ማልዌር ነው፡፡ ቫይረስ እራሱን ከተለያዩ ሶፍትዌሮች ጋር ባማጠባቅ እንደ ወርድ ዶኩሜንት ሊሆን ይችላል እኛ ፐሮገራሞቹን ስንከፍት እሱም አብሮ በመቀስቀስ የሚራባ ነው፡፡ በተጨማሪም ኔትዎርክ እና አንተርኔትንም ጨምሮ ማለት ነው፤ በፈላሽ ዲስክ፤ሜሞሪ ካርደ እና ሲዲዎችን በመጠቀም ይተላለፋል፡፡
 ቫይረስ እንደሌሎቹ ማዌሮችን ኮምውተራችን በመበከል ኮምውተራችን ፍጥነቱን ይቀንሳል፤ ዳታ ያጠፋል ዋይንም ይሰርቃል፡፡ ከበድ ያሉ ቫይረሶች የክፒውተራችንን ሃረድዋር ጭምር ሊጎዱ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ ሃረድ ዲስክን በመጉዳት ኦፐሬቲንግ ሲይሰተማችን ክራሽ እነዲዲርግ ያደርጋሉ፡፡ 

ወርም/Worm/ 

ወርሞች በአብዛኛው ተንሰራፍተው የሚገኙ ማዌሮች ናቸው፡፡ በኔትዎርክ አማካኝነት እራሳቸውን ችለው የኦፐሬቲንግ ሲይስተማችንን ድክመት በመጠቀም የሚባዙ ናቸው፡፡ ብዙ ጊዜ ኔትዎርክን በማጨናነቅ የእንተርኔት ፍጥነት ይቀንሳሉ ፤ የኮምፒውተራችን ፕሮሰሰር በአላስፋለጊ ትዛዞች በማጨናነቅ ኮምውተራችን ቀርፋፋ ያደርጋሉ፡፡
ከቫይረስ ጋር የሚለያቸው ወርሞች የሰዎችን ድጋፍ ሳያስፈልጋቸው እራሳቸውን ማባዛት ከመቻላቸው በላይ በኢሜሎች አታች ተደርገው ወደ ኮምፒውተራችን ሊገብ ይችላሉ፡፡ ቫይረስ ግን ለመባዛት የግድ እኛ የተበከለውን ፍላሽ ዲስክ መክፈት ይንም የተበከለ ወርድ ፋይል መክፈት ይኖርብናል፡፡ 

በማልዌር የተጠቁ ኮምፒውተሮች የሚያሳያቸው ምልክቶች 

ማልዌሮች የሚያደርሱት ጉዳት እና ምልክት እንደ ማልዌሩ አይነት፤እንደ ኮምፒውተሩ አይነት እና እነደ ሚጠቀመው የ ኦፐሬቲንግ ሲሰይሰም ቢለያይም አብዛኛው ጊዜ ግን አንድ ኮምፒውተር በማልዌር ሲጠቃ ከስር የተገለጹትን ምልክቶች ያሳያል

  • የኮምፒውተር ፍጥነት መቀነስ 
  • የኢንተረኔት ፍጥነት መቀነስ ( የኢንተርኔ ፍጥነት የቀነሰው ከ ኢንተርኔ አገልግሎት ከሰጠን አካል አለመሆኑን እረግጠኛ መሆን የኖርብናል) 
  •  የዌብ ብራውሰራችን ማዝገም 
  • ከእኛ እውቅና ውጪ በተለያየ ስም የተፈጠሩ ፈይሎች ወይን የተደበቁ ፋይሎች 
  •  የማናውቀው አይኮን ዴስክቶፓችን ላይ ሲገኝ 
  •  ፕሮገራሞች ካለእኛ ትዛዝ ሲከፈቱ ወይንም ሲዘጉ 
  •  እኛ ያላክነው ኢሜይል ተልኮ ከሆነ 
  •  ፌስቡክ ላይ እኛ ፖስት ያላደረግነው እና ካልታወቀ ምንጭ በእኛ ስም ፖስት የሚደረግ ከሆነ 
  •  የዴስክቶፕ ከለር መዛባት 
  •  አንዳድ ፕሮገራሞች አልከፍት ማለት በተለይ ታስክ ማናጀር አልከፈት ካለ ኮምፒውተራችን በማልዌር ተጠቅቶ ሊሆን ሰለሚችል ከተች የተገለጹትን መፍትሄዎች መተግበር ያስፈልጋል

 እርምጃዎች እና ጥንቃቄዎች 

ማልዌሮች ኮምፒውተራችንን በመበከል አደጋ ከማድረሳቸው በፊት አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ የሚፈጠረውን ችግር በከፍተኛ መልኩ መቀነስ ይቻላል፡፡ አንዴ ገብተው ጉዳት ካደረሱ በኋላ ግን ወደኋላ መመለስ በጣም አዳጋች ነው የሚሆነው ስለዚህ ቅድመ ጥንቃቅ ማድረገ የተሸለ አማራጭ ነው፡፡ 
  •  ምንጊዜም አንቲቫይረስ መጠቀም 
  •  የምንጠቀምባቸው አንቲቫይረሶች ተአማኝነት ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርብናል 
  •  በተቻለን መጠን አንቲቪረሳቻንን አፕቱዴት ማድረግ 
  •  ቀላል የሆኑ በነጻ ዶወንሎደ አድርገን የምንጠቀምባቸው አንቲቫይረሶቸ 
ዳውንሎድ የምናደርገው ሶፍትዌር በተለይ ቶረንት ፋይሎችን ከመክፈታችን በፊት ስካን ማድረግ ከማናውቀው አካል በኢሜላችን የሚላኩ የተላያዩ ዳውንሎድ ሊንኮችን ከመክፈት መቆጠብ ፤በተወሰነ ጊዜ ልዩነት ኮምፒውተራችንን ፉል ስካን ማድረግ፡፡



ምንጭ ከተለያዩ ዌብሳይቶች
 

0 comments:

Post a Comment

ShareThis