የኮምፒውተር ቨይረስ /Malware/ ምንድነው ? ክፍል አንድ


Malware ሚለው ቃል የመጣው Malicious Software የሚለውን ሁለት ቃል እንድላይ በመጭመቅ ነው፡፡ ቀጥታ ትርጉሙም ጎጂ ሶፍትዌር ማለት ነው፡፡ 
ማልዌር ወይም በተለምዶ እኛ ቫይረስ የምንለው በኮምፒውተር ቋንቋ የተፃፈ ኮድ/ሶፍትዌር ሲሆን ከእኛ እውቅና ውጪ ኮምፒውተራችን ላይ ተጭኖ ከፍላጎታችን በተጣፃረረ መንገድ የሚሰራ ነው፡፡ ማልዌር የኮምፒወተራችንን አስራር ያውካል ፤ያንቀራፍፋል፤ ዳታ የጠፋል ወይንም ይደብቃል፤ መረጃ ይሰርቃል ባጠቃላይ ኮምፒውተራችን ከእኛ እውቅና ውጪ ስርአቱን በማዛባት ጉዳት ያደርሳል፡፡ 
ማልዌር ሰፋ ያለ እና የጅምላ ስያሜ ነው ፡፡ ከማዌር አይነቶች ውስጥ ጥቂቶቹን አናያለን፡፡ 

አድዌር /Adware: Advertising-supported Software/ 

ይህ ማልዌር ከተላያየ ዌብሳይቶች ጋር አብሮ የሚመጣ ሲሆን ከእኛ ፍቃድ ውጭ ማስታወቂያዎችን
ሚያሰራጭ ነው፡፡ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን እንዳን የዳውንሎደ ዌብሳይቶችን ስንጠቀም ከእኛ ፍላጎት ውጪ በአዲስ ታብ ወይንም አዲስ ዊንዶው ያለፈላጎታችን ማስታወቂያ ሚከፈትበት ነው፡፡አኝህ የሚከፈቱ ማስታወቂያዎች መንም እንኳን ለዌብሳይቱ የገቢ ምንጭ ቢሆኑም አንዳነድ ጊዜ ግን ማዌልሮችን ያስተላልፋሉ፡፡
አንዳንድ ነፃ ሶፈተዌር ስንጭን ደግሞ አብረው በግዴታ ወይንም በተጠቃሙው ቸልተኝነት ህጋዊ ሶፍትዌር መስለው ይጫናሉ፡፡ ታዲያ በምን መልክ ነው ኮምፒውተራችን የሚጎዱት?
  • የኢንተርኔት ብራውሰራችን (ሞዚላ ፋየር ፎክስ፣ኦፔራ፤ኢንተርኔት ኤክስፕሎረር) አላስፈላጊ ጫና በማሳደር የኢነተሬን ፍጥነት ይቀንሳሉ 
  • ስለምንጎበኛቸው ዌብሰይ መረጃ ላመረታቸው አካል ይልካሉ
  •  ከፍላጎታችን ውጪ በግዴታ የማንፈልገውን ማስታወቂያ ያሳዩናል (ወሲብ ነክ ሊሆኑ ይችላሉ)

ራንሰምዌር /Ransomware : Ransom Software/ 

ራንሰም ዌር ቀጥታ ትርጉሙ አጋች ሶፍትዌር ማለት ነው፡፡ ኮምፒውተራችንን በማገት ለማስለቀቅ ክፍያ የሚጠይቅ ነው፡፡ 
ለምሳሌ ወርድ ዶክመንቶችን ብቻ ‘ኢንክርይፕት’ (ዳታ መቆለፊያ መንገድ ነው) በማድረግ ለመክፈት ገንዘብ ይጠይቃል ወይንም ደግም ጭራሽ ኮምፒውተሩን በመቆለፍ ወይንም በማገት ክፍያ የሚጠይቅ ነው፡፡ ይህ ማልዌር አንዴ ኮምፒውተራችን ካገታ በኋላ እንደነበረ ለመመለስ በጣም አዳጋች ሊሆን ይችላል፡፡ 

ሩትኪት /Rootkit/ 

ሩትኪት የሚባሉት ማልዌሮች የኮምፒውተራችን ዋናው መቆጣጠሪያ ክፍልን በማጥቃት ኮምፒወታረችን የሚቆጣጠሩ ናቸው፡፡ አንዴ ከተጫኑ በኋላ ያመረታቸው አካል ከርቀት ሆኖ በኢንቴርኔት አማከኝነት ኮምፒውተራችን መቆጣጠር ያስችለዋል ማለት ነው፡፡ የማልዌሩ ባለቤት ከእኛ እውቅና ውጪ ሴቲንጎችን ከርቀት ማሻሻል፤ ዳታ መስረቅ፤ ማጥፋት ክፍ ሲልም ካለበት ቦታ ሆኖ በእኛ ኮምፒውተር አማካኝነት የተለያዩ ወንጀሎችን መፈፀም ይችላል፡፡ ከአሰራራቸው ረቂቅነት የተነሳ ሩትኪቶችን ማደን ካበድ ነው፡፡

 ስፓይዌር /Spyware: Spying Software/ 

ስፓይዌሮች በዋናነት ተግባራቸው ኮምፒውተራችንን እንቅስቃሴ ልቅም አድረገው በመሰለል ለባለቤታቸው መላክ ነው፡፡ የሚልኩት መረጃ እንደ ስፓይዌሩ አይነት ቢለያይም የምንጎበኘውን ዌብሳይት፤የምንጠቀመውን ብራውሰር; ኦፐሬቲንገግ ሲስተም ምን እንደሆነ፤ ውቤሳይቶች ላይ የምንሞላውን ፎርሞች ኢሜል እና ፓስዎረድን ጨምሮ የምንጽፈውን ፊደላት ሳይቀር መዝግበው ይልካሉ፡፡ 



ትሮጃን /Trojan Horse/ 

ትሮጃኖች ብዙ ጊዜ ህጋዊ ሶፈትዌሮች መስለው የሚጫኑ ናቸው ፤አንዳነዴም እኛ እራሳችን ቀጥታ ዳውንሎደ አድርገን የምንጭናቸው ናቸው፡፡ተግባራቸው ከ ስፓይዌር እና ሩትኪት ጋር ተመሳሳይ ሲሆን የሚለያቸው ኮምፒውተራችንን የሚበክሉበት መንገድ ነው ፡፡



ምንጭ ከተለያዩ ዌብሳይቶች
 

0 comments:

Post a Comment

ShareThis