ከ YouTube ላይ ቪዲዮ ዳውንሎድ ማድረግ


ከ YouTube ላይ ቪዲዮችን ዳውንሎድ ለማድረግ የሚያገለግሉ ብዙ ሶፍትዌሮች ኢንተርኔት ላይ ይገኛሉ፡፡ አንዳዳቹን በነፃ ሌሎቹን ደግሞ በክፍያ ነው ዳውንሎደ የሚደረጉት፡፡ ቪዲዮችን ዳውንሎድ ከማድረጋችን በፊት ዳውንሎድ የምናደርግበትን ሶፍትዌር እራሱ ዳውንሎድ ማድረግ ወይንም ከሌላ ኮምፒውተር ላይ ኮፒ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ 


ዳውንሎድ ማድረግ ወይንም ማውረድ ማለት ምን ማለት ነው?

ማንኛውንም አይነት ፋይል (ቪዲዮ፤ድምጽ፤ጽሁፍ፤ስእል ….) ከኢንተርኔት ላይ ወደ ኮምፒውተራችን ኮፒ የምነዳርገበት መንገድ ዳውንሎድ ይባላል፡፡ ምሳሌ፡ ከ YouTube ላይ ቪዲዮ ስናወርድ/ዳውንሎድ ስናደርግ ቪዲዮውን ከ ዌብሳይት ላይ ወደ ኮምፒውተረችን ኮፒ አደረግን ማለት ነው በተመሳሳይ መጽሀፍት፤ፊልሞች ወይንም ጌሞችን ከኢንተርኔት ላይ ወደ ኮምፒውተራችን ኮፒ ስናደርግ ዳውንሎደ አደረግን ማለት ነው፡፡ 

ከ YouTube ላይ ቪዲዮችን ለማውረድ/ዳውንሎደ ለማድረግ ተጨማሪ ለዳውንሎድ ማድረጊያ ተብለው የተዘጋጁ ሶፍተትዌሮች ያስፈልጉናል፡፡ ከ ለማውረድ ከሚያገለግሉ ሶፈትዌሮች መከካል Internet Download Manager (IDM) በብዙዎች ዘንድ ተመራጭ ነው፡፡ ግን እሱ ብቻ ነው ዳውንሎደ ማድረጊያ ማለት አይደለም፡፡ በዛሬው ቱቶሪያላችን ከ ደውንሎደ መማድረጊያ ሶፍትዌሮች ሶስቱን እናያለን፡፡ 

Internet Download Manager (IDM)

በብዙዎች ዘንድ ተመራጭ እና ተወዳጅ ነው ፡፡ከቪዲዮ ባሻገር የተለያዩ የፋይል አይነቶችን ዳውንሎድ ማድረግ ይችላል፡፡ ነፃ ሶፍትዌር አይደለም ፡፡ይህን ሶፍትዌር የሚያመርተው ድርጅት ሶፍትዌሩን ለ 30 ቀን የሙከራ ጊዜ ይሰጠናል ከተባለው ቀን በኋላ ከተመቸን እንድንገዛ ካልተመቸን ደግሞ ከኮምፒውተራችን እንድናሰስወግደው አድርጎ ነው የሚሰራው፡፡እንደ ሶፍትዌሩ አምራች ከሆነ ኮምፒውተራችን ላይ ከተጫነ ከ 30 ቀን በላይ አያገለግለንም ማለት ነው፡፡ በእኛ ሀገር ሁኔታ በኢንተርኔት አማካኝነት መገበያየት ስለማንችል ያለን አማራጭ ሶፍትዌረን ለ 30 ቀን ተጠቅመን ማስወገድ ወይንም ሶፍትዌሩን ክራክ በማድረግ የአግልግሎት ጊዜውን ማስቀጠል ነው፡፡እዚህ ጋር ክራክ ማድረግ ማለት ሶፍትዌሩን ሳንገዛው አንደ ገዛነው ማድረግ ማለት ነው፡፡

 የ  IDM አጫጫን 

1. መጀመሪያ IDM ዳውንሎድ ያድርጉ (IDM የሚለውን ክሊክ በማድረግ ዳውንሎድ ያድርጉ)
2. ብራውሰራችንን እንዝጋ 
3. ዚፕ ፈይሉን ይክፈቱት ከዛም ኤክስትራክት የድርጉት 
4. Setup የሚለውን አቃፊይክፈቱ
5.  idman615 የሚለውን እንደገና ይክፈቱ
6. Accept ሚለውን ይምረጡ
7. ኢንስታሌሽኑ አስኪያልቅ ድረስ Next የሚለውን መጫን
              * ክራክ እንዴት እንደምናደርግ Installation የሚለውን በመክፈት ማንበብ ይቻላል
ዳውንሎድ አደራረግ

የተለያዩ አይነት ፋይሎችን ማውረድ እንደሚችል ጠቅሰናል እንደ ምሳሌ ግን የምናየው ቪዲዮ ፋይሎችን እንዴት እንደምናወርድ ነው፡፡

 1. YouTubeን እንከፍታለን
 2. የምንፈልገውን የቪዲዮ ስም በመፈለጊያ ሳጥን ውስጥ እንፃፍለት ቀጥሎም Search ውይንም ኢንተርን መጫን
 3. ከሚመጡት የቪዲዮ ዝርዝሮች መካከል የምንፈልገው ላይ ክሊክ በማድረግ መክፈት
4. ቪዲዮው ሎድ አድርጎ መጫወት ሲጀምር ከቪዲዮው ማጫወቻ ሳጥን ከላይ በቀኝ በኩል Download video የሚል ይመጣልናል ቀጥሎም የምንፈልገውን የፋይል አይነት በመምረጥ Start now ማለት ነው 5. ዳወነንሎድ አደርጎ አእስኪጨርስ እንደ ፋይሉ መጠን እና እንደ ኢንተርኔቱ ፍጥነት ጊዜ ይወስዳል 6. ዳውንሎደ አድርጎ ሲጨርስም መጨረሱን ይገልጽልናል
7. እኛ ካልቀየርነው በስተቀር ዳውንሎድ የሚያደርጋቸውን ፋይሎች በ Downloads ፎልደር/አቃፊ ውስጥ ነው የሚያስቀምጠው ፤ ለጊዜው ዳውነሎደ ያደረግነው ቪዲዮ ስለሆነ ዳውንሎደ የደረግነውን ፋይል የምናገኘው Downloads ---> Videos የሚለው ፈልደር ውስጥ ይሆናል ማለት ነው፡፡

Free Download Manager (FDM)

FDM እንደ IDM ዳውንሎደ ለማድረጊያ ሶፍትዌር ነው፡፡ በነፃ ደውንሎድ የሚደረግ ሲሆን እስከፈለግነው ጊዜ ድረስ ከራክ ማድረግ ሳያስፈልገን የምንጠቀምበት ሶፍትወዌር ነው፡፡

 FDM ከ IDM የሚለየው በነፃ የሚገኝ መሆኑ እና በተጨማሪ የ ቶረንት ፋይሎችን ማውረድ መቸላ ነው፡፡ ስለ ቶረንት ፋይሎች በሌላ ቱቶሪያል አሳያችኋለው፡፡ 

FDMን ከ www.freedownloadmanager.com ላይ በቀጥታ በመግባት Download የሚለውን ታብ በመጫን የምንፍልገውን ቨርሽን ዳውንሎድ ማድረግ እንችላለን፡፡ ዳውንሎደ አድርገን ከጨረስን በኋላ ከላይ ለ IDM በተጠቀምነው መንገድ በተመሳሳይ ሁኔታ ኢንስታል ማድረግ፡፡ ኢንስታል አድርገን ከጨረስን በኋላ ልክ እንደ IDM፤ YouTube በመክፈት የምፈልገውን ቪዲዮ ከከፈጥን በኋላ ከቪዲዮ ላይ በግራ ጠርዝ በኩል Download የሚል ያመጣልናል እሱን ክሊክ በማድረግ ዳውነሎዱን ማስጀመር፡፡፡ ዳውንሎድ አድርጎ ሲጨርስ በተመሳሳይ መልኩ ዳውኖዳችንን መጨረሱን ይገልጽልናል፡፡
XiloSoft YouTube Downloader 

ይሄኛው ሶፍትዌር ስራው YouTube ብቻ ቪዲዮችን ዳውንሎደ ማድረግ ነው፡፡ በነፃ ዳውንሎድ የሚደረግ ሲሆን ከተጫና በኋላ እንደ ቀደምቶቹ ቨዲዮችን በብራውሰራችን ፈልገን ሳይሆን የምናወርደው በራሱ በሶፍትወሩ በመጠቀም ነው፡፡

 XiloSoft YouTube Downloader (ክሊክ ያድርጉት )  ዳውንሎደ በማድረግ ከላይ በተጠቀሱት መንገድ ኢንታል ማድረግ፡፡ ዴስክቶፓችን ላይ የተፈጠረውን XiloSoft YouTube Downloader ሾርትከት መክፈት ወይንም በተለመደው አካሄድ All Programs በመግባት መክፈት የቻላል ፡፡ ቀጥሎም ሶፍተዌሩ ውስጥ በሚገኘው የመፈለጊየ ሳጥን ውስጥ የምንፈልገውን ቪዲዮ ስም በመፃፍ ቪዲዮችን መፈለግ፡፡ የምንፈልገውን ቪዲዮ መርጠን ማጫወት ስንጀምር ከለያ ሜኑ ባር ላይ ከተዘረዘሩት ምልክቶች መካከል መጀመሪያ ላይ የሚገኘውን የወደታች ቀስት መጫን ቅስቱን ስንጫን በቀጥታ ዳውንሎድ ማድረግ ይጀምራል ማለት ነው፡፡ የዳውንሎዳችንን ሁኔታ ለማየት በግራ በኩል ከተዘረዘሩት ሜኑዎች ውስጥ Downloads የሚለውን በመጫን ምን ላይ እንደ ደረሰ ማወቅ ይቻላል ሲጨርም መጨረሱን ይነግረናል፡፡ በተጨማሪ አንዱ ዳውነሎድ ሳያልቅ ሌሎችን ማሰጀመርም ይቻልል፡፡

0 comments:

Post a Comment

ShareThis