F1 – F12 ቁልፎች አገልግሎት

በኮምፒውተራችን ኪይቦርደ ከላይ ተደርድረው የምናገኛቸው ከF1 – F12 ያሉ ቁልፎችን Function Key እንላቸዋለን፡፡ በዋናነትም ከሌሎች ቁልፎች ጋር በማጣመር እንደ አቋራጭ እንጠቀምባቸዋለን፡፡ እንኘህ ቁልፎች እንደ ምንጠቀመው የ ኦፐሬቲንግ ሲስተም እና ሶፍትዌሮች አገልግሎታቸው ይለያያል፡፡: በዛሬው ቱቶሪያላችንም የተወሰኑትን እናያለን፡፡ 

F1 

ብዙ ጊዜ የምንጠቀመው እርዳታ ስንሻ ነው፡፡ በአብዛኛው ሶፍትዌሮች F1 ስንጫን የ Help መስኮትን ይከፍቱልናል፡፡ ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን Start እና F1 መጫን የ Microsoft Online Help ይከፍታል፡፡ 

 F2 

የተመረጠን አይከን፤ፋይል ወይንም አቃፊ ስም ለመቀየር F2 መጫን ይቻላል፡፡ ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን Alt + Ctrl + F2 መጫን የ Open መስኮትን ይከፍታል፡፡፡ 

F3 

ዴስክቶፕ ላይ ካን ስንጫን የፍላገ መስኮት ይከፈታል፡፡ ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን ቃልን መርጠን Shift + F3 መጫን የተመረጠው ቃል ውስት የሚገኙ ፊደላትን አንድላይ ካፒታል ወይን ስሞል ወይንም የመጀመሪያውን ፊደል ካፒታል ያደርግልናል፡፡ 

F4 

አሁንም ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን F4 መጫን ለመጨረሻ ጊዜ የተገበርነውን ይደግምልናን፡፡ ለምሳሌ አበበ ብለን ብንጽፍ እና F4 ብናጫን በ የምትባለውን ፊደለ በድጋሚ ይጽፍልናል፡፡Alt + F4 መጫን አክቲቭ የሆነውን መስኮት ይዘጋልናል፡፡ Ctrl + F4 ስንጫን ደግሞ አክቲቭ ከሆነው መሰኮት ውስጥ አክቲቭ የሆነውን ታብ ይዘጋልናል፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው በ ብራውሰራችን ከአንደ በላይ ታብ ከከፈትን Ctrl + F4 ስንጫን ያለንበትን ታብ ብቻ ይዘጋልናለን ነገር ግን Alt + F4 ብንጫን ሙሉ በሙሉ ብራውሰሩን ይዘጋብና ማት ነው፡፡ 

F5

 አሁን ገበያ ላይ ባሉት አብዛኛዎ ብራውሰሮች ላይ F5 መጫን Refresh ያደርገልና፡፡ ማይክሮሶፈት ወርድ ላይ የ Find መስኮትን ይከፍትልናል፡፡ ማክሮሶፍት ፓወር ፖይንት ላይ ደግሞ Slideshow ያስጀምርልና፡፡ 

F6 

በአብዛኛው ብራውሰሮች ላይ F6 ስንጫን የማውሳችን አቅጣጫ መጠቆሚያ(cursor) ወደ አድራሻ መጻፊያው ይወስድልና፡፡ ከአንድ በላይ የማይከሮሶፍት ወርድ ከከፈትን Ctrl + Shift + F6 መጫን ወደቀጣዩ የማይክሮሶፍት መስኮትያሸጋግረናል፡፡ 

F7

 ማይክሮሶፍት ወረድ ላይ Shift + F7 መጫን የ Thesaurus መስኮትን ይከፍትልናል የሚያገለግለውም ሰፔሊንግ፤ ፍቺ እና ሰዋሰው ለማስተካከል ነው፡፡ 

F8 

ኮምፒውተራችን ሲነሳ የ Windows፤ Startup menu ለመግባት የጠቅማል፡፡ 

F10

 አክቲቭ የሆነውን ዊንዶው ሜኑ ባርን አክቲቭ ለማድረግ ያስችላል፡፡ Shift + F10 መጨን ራይት ክሊክ እንደማድረግ ይቆጠራል፡፡ 

F11

 በአብዛኛዎ ብርውሰሮች ላይ F10 ስንጫን የምንመለከተው መስኮት ሙሉ በሙሉ የኮምውተራችንን ስክሪን ይሞላዋል (Full screen) ፡፡

 F12 

ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ የ Save as ማስኮትን ይከፍትልናል፡፡ Ctrl + Shift + F12 ፐሪንት ያዛል፡፡

0 comments:

Post a Comment

ShareThis