የኢሜይል ደህንነት ቲፖች


ከዚህ በታች የምገልጽላችሁ ነጥቦች ኢንተርኔት ስጠቀሙ በተለይ ኢሜይሎች እና የማህበራዊ ገጾችን ስትጠቀሙ ደህንነታችሁን ለመጠበቅ የምትጠቀሙብትን መንገዶችን ነው፡፡

 1. የምንጠቀመውን ኢመይል ከሰልካችን ጋር በማገኛኘት የ 2 step verification አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን የህም ማlት ኢመይላችን ወይንም ፌስቡካችንን ከመግባታችን በፊት ምንጊዜም የ ድምጽ ወይንም የ አጭር መልእክት ጽኁፍ በስለካችን ይደርሰናል፡፡ቀጥሎም የተላከለን የማረጋገጫ ኮድ ካስገባን በኋላ ወደ ኢሜላችን ወይንም ፌስቡካችን እነገባለን ማለት ነው፡፡ ይህ የሚጠቅመን ከእኛ ውጪ ማንም ሰው ፓስዎረዳችንን ቢያውቅ እንኳን ካለ ስልካችን ወደ አካውንታችን መግባት አይችልም ማለት ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ ስልካችን ምንጊዜ ከእኛ ጋር ይሆናል ተብሎ ስለሚታሰብ ሌላ ሰው በሌላ አካባቢ እንኳን አካውንታችን ለመክፈት ቢሞክር በስለካችን በኩል በሚመጣው መልእክት ማወቅ እንችላን፡፡ በተጨማሪም ፓስዎረዳችንን ብንረሳ የማረጋገጫ መልእክ በቀላሉ በስልካችን ይላክልናል፡፡ የጂሜይል እና የፌስቡክ የ 2 step verification እነዴት እንደሚደረግ በቀጣዩ እናያለን 

በግላችን ኮምፒውተር የምንጠቀም ከሆነ ደግሞ ከሌላ ኮምውተር ወይንም የስልክ ቀፎ ላይ በእኛን የፌስቡክ አካውንት ለመግባት ሙከራ ከተደረገ ወይንም ከእኛ ኮምፒውተር ውጪ ለመግባት ከፈለግን በስልካችን የማረጋገጫ መልእክት እንዲልክልን ማድረግ፡፡

 2. ፓስዎርዳችን ምንግዜም ረዘም በሎ ቁጥር ፤ቃላት እና ምልክቶች የተቀላቀሉበት እና በቀላሉ ሊገመት የማይችል ማድረግ 

3. ኢሜይል ስናወጣ ወይንም ካወጣን በኋላም መቀየር ይቻላል የ Security Questions የሚለውን ቦታ በጥንቃቄ በመሙላት ፓስዎረዳችንን ስንረሳ ማስተዋሻ ይሆነናል ሆንም ግን የምነሞላው መልስ በሌላ ወገን ሊገመት የሚችል መሆን የለበትም 

4. ምንጊዜም ወደ አካውንታችን ስንገባ አድራሻው በትክክል እኛ የምንፈልገውን መሆኑን ማረጋገጥ ይርብናል ምክኒያቱም እነደኛው የ ሀከሮች የመስረቂያ መንገዳቸው የሆነው የዌብሳይቶችን የማስመሰል መንገድ ስለሆነ፡፡ 

5. በህዝብ መገልገያ ቦታዎች ወይንም ኢንተርኔት ካፌ ውስጥ ስንጠቀም ሎግ አውት ማድረጋችንን አለመዘንጋት 

6. የግላችን ባልሆነ ኮምፒውተር ስንጠቀም ምንጊዜም የአካውንታችንን መረጃ ካስገባን በኃኋላ በራውሰሩ በተለያ መንገድ ፓስዎርዳችንን ሴቬ ለማድረግ ሲጠይቀን አንብበን እናዳያደርገው ማድረግ 

7. ፓስዎረዳችንን በተዋሰነ ጊዜ መቀያየር 

8. በኢሜይላችነ የሚላኩ አታችመንቶችን ከታማኝ ምንጩች ከሆኑ ብቻ ዳውንሎድ ማድረግ 

9. ኢንተርኔት ላይ የምናየውን የተሳሳቱ ግን አጓጊ የሆኑ ለምሳሌ Speed Up Your Pc፤ Clean Your Registry to Boos your PC፤ የሆነ ያል ቁጥር በመጥቀስ Problems found on your pc፤ scan your pc for malware ምናንምን የሚሉ ነገሮችን አለመክፈት ምክኒያቱም አብዛኛዎች አብረዋቸው አድዌር እና ስፓይዌር አብረው ይይዛሉ፡፡ 


0 comments:

Post a Comment

ShareThis