ዌብፔጆችን እንደ ፒዲኤፍ ሴቭ ማድረግ


ዛሬ የምናየው ቀላል የብራውሰር ትሪክ ነው፡፡ ጎግል ክሮምን በመጠቀም እንዴት ዌብ ፓጆችን እንደ ፒዲኤፍ ሴቭ እንደምናደርግ እናያለን፡፡ በተለይ ለሚነበቡ ይዘቶች ኦፍላይን ለማንበብ ፒዲኤፍ ተመራጭ ፈረማት ነው፡፡ 

አንዳንድ ጊዜ በተለይ ፅሁፎችን ሴቭ አድርገን ኢንተርኔት በሌለን ሰአት ለማንበብ እንቸገረላን፡፡ ምክንያቱም ፡ 

  • ዌብሳይቶቹ ሙሉ በሙሉ ሴቭ ላይደረጉ ስለሚችሉ 
  • ሴቭ ካደረግን በኋላ የዌብሳይቱን መጀመሪያ እንዳየነው ድጋሜ በተመሳሳይ መልኩ ስለማናየው (ብዙ ጊዜ አንድ ዌብሳይት ስንጎበኝ የምንያው ዳታ/ኮንቴንት ሙሉ በሙሉ እዛው ዌብሳይት ላይ አይገኝም ግን እኛ እንደ ጎብኚ ዌብሳይቱን ስንመለክት ሁልም ፊትለፊት የምናየው ነገር ሁሉ እዛው ዌብሳይት ላይ ያለ ይመስለናል ነገር ግን የምናየው ነገር ከተለያዩ ሰርቨሮች ሊንክ ተደረገው የሚመጡ ማስተወቂያዎች፤ስክሪፕቶች እና ወደሌላ ዌብሳይት የሚወስዱ ሊንኮች ናቸው፡፡ ምሳሌ ብዙ ዌብሳይቶች ላይ የምናያቻው ማስታወቂዎች በቀጥታ ዌብሳይቶቹ ላይ የተሰሩ አይደሉም የኢንተርኔት የማስታወወቂያ ኔትዎረክች እንጂ፡፡ስለዚህ መጀመሪያ የምናያው ዌብሳይት በእነዚህ እና በመሳሰሉት ነገሮች ተሞልቶ ነው ማለት፡፡ ቀጥሎ እኛ ሴቭ ከደረግነው በኋላ ኢንተርኔት በሌለበት ወቅት ስንከፍተው እነዛ በተጨማሪ ሊንክ የተደረጉት የተለያዩ ነገሮችን ያለ አንተርኔት ማየት ስለማንችል ዌብሳይቱን እንደነበረ ማግኘት ያስቸግራል፡፡ ከላይ ለተጠቀሱት እና ለተለያዩ ምክኒያቶች ዌብሳይቶችን እንደ ፐዲኤፍ ሴቭ ማድረግ ከፈለግን እንደሚከተለው እናደርጋለን ለጊዜው ይህ የሚሰራው ጎግል ክሮም ላይ ብቻ ነው፡፡ 

1. ጎግል ክሮምን እንከፍታለን

 2. ወደ ፐዲኤፍ ሴቭ ለማድረግ ወደምንፈልገው ዌብሳይት እንሄዳለን 

3. የምንፈልገውን ዌብሳይት ካገኝን በኋላ ኮንትሮል እና ፒን እንጫን (ፕሪንት)

 4. አሁን ‘ Destination ‘ ከሚለው በታች ‘ change ‘ የሚለውን በመጫን ‘ save as pdf ‘ የሚለውን እንጫን 

5. ከላይ ‘ Print’ ከሚለው ስር ‘ Total : X pages’ X በሚለው ፈንታ ዌብሳይቱ ሴቭ ሲደረግ ስንት ገፅ እንደሚሆን ይነግረናል ከሱ ስር ደግም ‘ Save’ የሚለውን በመጫን ሴቭ የምናደርግበትን ቦታ መርጠን ሴቭ ማድረግ፡፡

0 comments:

Post a Comment

ShareThis