ምርጥ ምርጥ የጎግል ቲፖች


በተለምዶ ከምናውቀው የጎግል መፈለጊያ ሳጥን ጀርባ ብዙ የሚገርሙ አጭር የመፈለጊያ ዘዴዎች አሉ፡፡ ከብዙ ጥቂቶቹን ላሳያችሁ
1. የታዋቂ አርቲስቶችን የስራ ልምድ ለማያት ምን ምን ፊልች ላይ እንደ ተሳተፉ ከነ አመተምህረቱ ለማየት ወይንም የዘፋኝን የዘፈኖች ዝርዝር ሁኔታ ለማየት በ አጭሩ የዘፋኙን ስም እና ስራውን መፃፍ፡፡ ለምሳሌ የማት ዴመንን ፊልሞች ለማየት Matt Damon movies በማለት በአንድ አረፍተነገር ብቻ የማት ዴመን ፊልሞችን ዝርዝር ማየ ይቻላል፡፡ በተመሳሳይ የ ዋን ሪፐብሊክን ዘፈኖችን ለማየት One Republic songs በማለት በተመሳሳይ ሁኔታ ማግኘት ይቻላል፡፡ በተጨማሪም የአለበም የዘፈን ዝርዝሮችን ለማየት የአርቲስቱን ስም በማስቀድም የአልበሙን ስም በመፃፍ በአልበሙ ውስጥ የተካተቱ ዘፈኖችን ማየት ይችላሉ፡፡ 



 2. ያልተለቀቁም የተለቀቁም ፈልሞች፤ ጌሞች ወይን አልበሞችን የሚለቀቁበትን/የተለቀቁበትን ቀን ለማወቅ ርእሱን በማስደም ‘Release date’ የሚል ሀረግ በመጨመር ቀኑን ማወቅ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ የ Titanic የተለቀቅበትን ቀን ከፈለኩ በጎገል መፈለጊያ ሳጥን ውስጥ Titanic Movie release date በማት የሚለቀቅበትን ቀን ማውቅ እንችላን፡፡ 


3. አጭር መረጃ ለማግኝ በቀጥታ የምንፈልገውን ሀረግ በመጻፍ ማግኘት ይቻላል ፡፡ ለምሳሌ የአንድ ከተማን ህዝብ ብዛት ለማወቅ የከተማውን ስም በማስቀደም ካዛ Population በማለት ከተማውን የህዝብ ብዛት ማወቅ ይቻላል፡፡ በተመሳሳይ ክስተቶችንም ለማወቅ በዚሁ በተመሳሳይ መንገድ ማወቅ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ የአንደ ታወቂን ሰው የሞተበትን ቀን ለማወቅ የሰውየውን ስም በማስቀደም ቀጥሎ death ብሎ በመጻፍ ማወቅ ይቻላል፡፡ በተመሳሳይ የተራራን ርዝመትን ለማወቅ ተራራውን ስም በመጥቀስ elevation በማለት ማወቀ ይቻላል፡፡ 


4. የእግርኳስ ጨዋታ ውድድር ውጤትን ለማወቅ በቀላሉ ከጨዋታው በኋላ (ጎግል በዚህ መልክ የሚያሳየው መረጃ ለመጨረሻ ግዜ የተደረገውን ነው) የቡድኑን ስም በመጻፍ score የሚል ቃል በመጨመር ውጤት ማየት ይቻላል


 5. የአንድ ከተማን የአየር ሁኔታን ለማወቅ የከተማውን ከተማ በማስቀደም weather ብለን በመጻፍ የአምስት ቀን አየር ሁኔታን ማወቅ ይቻላል፡፡


 6. በተለያ የሀገር የለውን ሰአት ለማወቅ የከተማውን ስም በማስቀደም time ብሎ በመፃፍ ማወቅ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ Addis abeba time



 7. ጎግልን እንደ ካልኩሌተር መጠቀምም ይቻላል ፡፡ የምትፈለጉትን ቁጥር እና የስለሌት ምልክት በ መፈለጊያ ሳጠን ውስጥ በማስገባት ውጤቱን ማወቅ ይቻላል፡፡


 8. ሥሌት ለመለካት ከፈለግን በተመሳሳይ የምንፈልገውን ለውጥ በመፃፍ መለስ ማግኘት እንችላን፡፡ ለምሳሌ 1km into mile ብለን በንፅፍለት ወዲያው 1 ኪ.ሜ. ስንት ማይል እንደሚሆን ሂሳን ሰርቶ ያሳያናል ማት ነው፡፡ የጎግል የልኬት መቀየሪያ ርቀት ብቻ ሳይሆን የተለያዩ አይነት መመዘኛዎችን መስራት ይቻላል፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ ቃላ ግን ለማወቅ ከበድ የሚሉ ለምሳሌ በአንድ አመት ውስጥ ስንት ሰከንዶችን እነዳሉ ለማወቀቅ በ መፈለጊያ ሳጥ ውስጥ Seconds in a year ብለን ብንጽፍ መጀመሪያ ላይ የሚያመጣልን ውጤቱን ይሆናል፡፡

 9. የተለያ ሀገር ገንዘብን ምንዛሬ ለማወቅ፡፡ ለምሳሌ 1 USD to Rupee (ይህን ቱቶሪያል ሳሰጋጅ የኢትዮጵያን ብር ዝርዝር ውስጥ አላገኘሁም)


 10. የቃላትን ትሩግም ለማወቅ (እንግሊዘኛን በእንገሊዘኛ) ወይንም ጎግልን እንደ ኦክስፎርድ ዲክሽነሪ ለመጠቀም define: ብለን እንዲፈተላን የምንፈልገውን ቃል መፃፍ፡፡ ለምሳሌ ውብሳይትን የቃል ትርጉም ለማወቅ define: website በማት የዌብሳይትን ትረጉም ማወቅ ይቻላል 11. የቃላት ትረጉምን በተለያየ ቋንቋዎች ለማወቅ ፡፡ ለምሳሌ Love የሚለውን ቃል በስፓኒሽ (የስፔን ቋንቋ) ለመቀየር ከፈለግን Translate love to Spanish ብለን በመፃፍ Love ማለት በስፔን ቋንቋ ምንእንደሚመስል ማወቅ ይቻላል፡፡ ብዙ አርፍተነገሮችን ለመተርጎም ካስፈለገ ወደ www.translate.google.com በመሄድ በአንድ ጊዜ ብዙ አረፍተነገሮችን ወደተለያየ ቋነቋ መቀየር ይቻላል፡፡




 12. የተለያየ ሀገር ማሪዎችን ለማወቅ፡፡ ለምሳሌ በዙም የማናቃትን ሀገር ኡዝቤኪሰታን ብንወስድ የኡዝቤኪስታንን ማሪ ስም ለማወቅ በ ጎግል የመረጃ መፈለጊያ ሳጥን ውስጥ Uzbekistan leader በማለት የሀገሪቷን መሪ ስም ማወቅ ይቻላል




ShareThis