ህክር/ሃኪንግ ማለት ምንድነው ? ክፍል 1


ሃከር የሚለው ቃል በአማርኛ ቀጥተኛ ፍቺ ባይገኝለትም ኤሌባ (ኤልክተሮኒክስ ሌባ) የሚለው ተመጣጣኝ ፍቺ  ሆኖ ሊያግባባን የችላል፡፡

ብዙ ጊዜ ዲጂታል እና ኤሌክትሮኒክስ የሆኑ በተለይም ባሁኑ ወቅት ኮመፒውተሮችን እና ለተለያየ አገልገሎት የተመረቱ መገልገያዎችን ከባለቤታቸው ወይንም ካመረታቸው አካል እውቅና ውጪ በተለያየ መንገድ ለተለያየ አገልግሎት ማዋልን ሃኪነግ እንልወላን፡፡ የድርጊቱን ፈጻሚ ደግም ሀከር እንለዋልን፡፡ ሰፋ ባለ መልኩ ስናያው ሃኪንግ ከግለሰቦች ጀምሮ በሃገራት ደራጃ የሚካሄድ ሲሆን ደራጀውም ክትንሽ ግለሰባዊ ጥቅም አንስቶ እስከ በሀገር ደረጃ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል፡፡


በዋናነት ሀከሮችን በሶስት ልንከፍላቸው እንችላለን

 ባለ ነጭ ቆብ

 እዚህ ምድብ ውስጥ የሚመደቡ ሀከሮች በዋናነት በድርጅት ውስጥ ተቀጥረው የኮመፒውተሮችን ደህነነት የሚፈትሹ ሲሆኑ አውቀታቸውን ለ ወንጀል ወይንም ለግል ጠቅም ሳይሆን ለመልካም ምርምሮች እና ለትላልቅ ፐሮጀክቶች ያሉባቸውን የደሀንነት ክፈቶችን እያጠኑ ማስተካከያ ያሚያደርጉ ናቸው፡፡ እነዚህ ባሙያዎች ብዙም ጊዜ በ ኮምፒወተር ደህንነት ድርጅት ውስጥ ተቀጥረው ይሰራሉ፡፡ 

ባለ ጥቁር ቆብ 

ብዙ ጊዜ መጥፎ ሃከሮች የምንላቸው ሲሆን ስራቸውም የ ግለሰቦችን ወይንም የድርጅቶችን ዳታ መስረቅ ወይንም ላልተገባ አላማ እና ለግል ጥቅም የሚየያውሉ ናቸው፡፡ እኚህ ሀከሮች በተለይ ኢኮኖሚያቸው በከፍተኛ ደረጃ ኢንፎረሜሽን ቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ሀገሮች ላይ ትልቅ ጉዳት ያደርሳሉ፡፡ ባንኮችን ይሰርቃሉ፤ የንግድ መሰጥር ያባክናሉ፤ ከፍ ሲልም የሀገር ደህንነት አደጋ ላይ ይጥላሉ፡፡ እነዚህ ሀከሮች ብዙ ጊዝ በግል ወይንም በቡድን ተደራጅተው ይንቀሳቅሉ፡፡ በአጭሩ ብዙ ጊዜ ጎጂ ቫየረስ የሚሰሩትን ባለ ጥቁር ቆብ ሰንል አንቲ ቫይረስ የሚሰሩትን ደግሞ ባለ ነጭ ቆብ ልንላቸው እንችላለን፡፡ 

ባለ ግራጫ ቆብ 

እኚህ ሀከሮች በሁለቱ መሃል የሚገኙ ሲሆኑ እውቀታቸውን እነደ ሁኔታው ለጥሩም ወይንም ጥሩ ላልሆነ ተግባር የሚያውሉ ናቸው፡፡ 

እዚህ ላይ መገንዘብ ያለብን ጥሩ ወይንም መጥፎ የሚለው ትርጉም እንደ ቦታው እና ሁኔታው ሊለያይ ይችላል፡፡ ለምሳሌ በመንግስት ተቀጥረው ግን ደግሞ የገለሰቦችን መብት በተጻረረ መልኩ የሚሰልሉ ሀከሮች በመንገስት ጥሩ ቢባሉም በዜጎች ደግሞ ጎጂ ሊባሉ ይችላሉ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ አንዳዴ ሃከሮቹ ከተነሱበት ሀሳብ አቅታጫም እነደሁኔታው በተለያያ አካል መጥፎም ጥሩም ሊባሉ ይችላሉ፡፡

 የ ሀከሮች ደረጃ

 ለማጅ 

እኝህ ሀከር ነን ባዮች ሲሆኑ ከእውነተኛ ብቃታችው ፍላጎታቸው የሚበልጥ ሲሆን ብዙም ጊዜ የራሳቸው የሆነ ቴክኒከ ወይንም ሶፈትዌር የሌላቸው ሲሆን በተለያያ መንገድ ያገኟቸውን እውቀቶች በመጠቀም ወይንም ያሉትን የደህንነት ክፍተቶችን በመጠቀም ሃክ የሚያደርጉ ናቸው፡፡ 

መካከለኛ  

እነዚህ ሀከሮች ከ ለማጆች የሚለዩት ያሉትን የደህነነት ከፍተቶች በደንብ አጥንተው የሚያወቁ ሲሆኑ በተጨማሪም ለተላያያ አገልገሎት የተሰሩ ሶፍትዌሮችን በመጠቀም ሃክ የሚያደርጉ ናቸው፡፡ እኚህ ሀከሮች ሚጠቀሙበትን ሶፈተዌር ጠንቅቀው ያወቃሉ ማለትም ሶፈተዋሩ ከበስተጀርባ ምን እየሰረራ እንደሆን የሚረዱ ናቸው ነገር ግን ጀማሪ ሀከሮች ለሃኪንገ የሚውሉ ሶፈተዋችን መጠቀም ቢችሉም ፊተ ለፊት ከሚመጣው ውጤት በስተጀርባ ምን እየተካደ እንደሆነ ብዙ ጊዝ አይረዱም፡፡ 

ፐሮፌሽናሎች 

እኚህ ሀከሮች የሚጠቀሙበትን ሶፈተዋሮች አብዛያውን ጊዜ እራሳቸው ይጽፋሉ ወይንም ነባር ሶፍትዌሮችን በሚመቻቸው መልኩ ያሻሽላሉ፡፡ ቫይረስ ወይንም አንቲ ቫይሩስ ይሰራሉ፤ እንደ ባህሪያቸው ባለ ነጭ ወይንም ባለ ጥቁር ቆብ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ይህም ማለት በ ግለሰብ ደረጃ ዋንም ተቀጥረው አሊያም ለማንግስታት ሊሰሩ ይችላሉ፡፡

0 comments:

Post a Comment

ShareThis