ምርጥ ምርጥ የ Windows ቲፖች

 
Problem Steps Recorder 

ይህ አቋራጭ ከ WINDOWS ኮምፒውተራችን ጋር አብሮ የሚመጣ ግን የማንጠቀምበት አሪፈ አቋራጭ ነው፡፡ የሚያገለግለውም በተለይ ኮምፒውተራችን ችግር ሲገጠመው የኮምፒውተራችንን ስክሪን በመቅዳት ቅጂውን በቀላሉ ለማሳየት ያገለግለናል፡፡ ይህን ፕሮገራም ለማስጀመር Run በመክፈት (ለመክፈት Start + R ወይንም Start ላይ ከሚመጡ ምርጫዎች ውስጥ በስተቀኝ በኩል ይገኛል) ቀጥሎም psr ብለን በመፃፍ Ok ማለት፡፡



ከላይ የምታዪት ምስል ሲመጣ Start Record የሚለውን በመጫን እንዲቀዳ የተፈለገውን ስራ ማከናወን ስንጨረስ Stop Record የሚለውን በመጫን ቀጥሎም የቀዳነውን የምንፈልግበት ቦታ ላይ ሴቭ አድርገን መመልከት እንችላለን፡፡ ሴቭ የሚሆንል በ Zip ፎረማት ሲሆን የሚከፍትልን ደግሞ በ ብራውሰራችን ነው፡፡ የቀዳነውን ክንዋኔ በምስል በማስደገፍ የሳያናል፡፡

ከምፒውተራችንን ማፍጠን

ብዙ ጊዜ ለኮምፒውተራችን በፍጥነት አለመነሳት ምክኒያት የሚሆነው ኮምፒውተራችን ሲነሳ ብዙ ፕሮግራሞቸ አብረው ስለሚነሱ ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜም የማንፈልጋቸው ፕሮግራሞች ከኮምፒውተራችን እኩል በመነሳት ያቀራፈፉታል፡፡ እንዚህን አላሰፈላጊ ፕሮገራሞች ከአኛ ፍቃድ ውጪ ከኮምፒውተራችን እኩል እንዳይነሱ ለማድረግ ወይንመ ለማስቆም የሚከተለውን ቀላል አቋራጭ እንጠቀማለን፡፡
የRun ሳጥንን በመክፈት msconfig ብለን እንፃፍ ቀጥሎም Ok ፡፡: ከሚመጣለን ትንሽ መስኮት Startup tab የሚለውን እንምረጥ በዛ ስርም ኮምፒውተራችን ሲነሳአብረው የሚነሱ ፕሮግራሞች ዝርዝር እንመለከታለን የማንፈልገውን መርጠን Disable ማድረግ በዚህም መንገድ የኮምውተራችን አነሳስ ፍጥነት መጨመር እንችላለን::

Windows God Mode

 Windows፤ God Mode የሚባል የተደበቀ አቃፈ አለው፡፡ ይህ አቃፊ የ ኮምውተራችን ጠቅላላ የለውጥ ስርአት በእንድ ላይ የያዘ ነው፡፡ ይህን አቃፊ በመክፈት ማንኛውን አይነት ለውጥ ማድረግ እንችላን ፡፡
Windows God Modeን ለማምጣት አዲስ ኣቃፈ በመምረጥ ስሙን God Mode.{ED7BA470-8E54-465E-825C-99712043E01C} ማድረግ ( ኮፒ ፔስት ማድረግ) እንደጨረሱ ኢንተርን መጫን ይህንጊዜ የአቃፊው ምልክት ወደ Control Panel ምልክት ይቀየራል፡፡ አዲስ የፈጠርነውን God Mode የተባለውን ምልክት ስንከፍተው ማንኛውንም ለውጦች ለማድረግ የሚያስፈልጉ የ መቼት (Setting) ዝርዝር እናገኛለን የፈለገነውን መርጠን ማከናወን፡፡
ይህ God Mode ሁልንም የኮምፒውተራችን የለውጥ ትእዛዙች የያዘ ስልሆን መጠንቀቅ ይኖርብናል በመጀመሪያም የተደበቀው ለደህንነታችን ሲባለል ስለሆነ የምናደርገቸውን ለውጦች በመጀመሪየያ ማወቅ ይጠበቅብናል፡፡

ድምፅ እና ምስል ማስተካከል

አንዳነዴ የተለያዩ ቪዲዮችን ስናጫውት ቪዲዮ እና ድምጽ ሳይጣጣም ይቀራል ይህን ጊዜ J ወይንም K በመጫን ድምጹን ወደኋላ ወይንም ወደ ፊት ማምጣት ይቻላል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ሰብታይትልም አልጣጣም ብሎ ካስቸገረን H እና G በመጫን ወደፊት እና ወደኋላ ማሳለፍ ይቻላል፡፡ ይህ የሚሰራው ግን VLC Media Player ላይ ብቻ ነው፡፡

Typing Tricks 

የተለያዩ ፅሁፎችን ሰንፅፍ የተሳሳትነውን ቃል ለማጥፋት እያንዳንዱን ፊደል ለየብቻ Backspace በመጫን ከማጥፋት Ctrl እና Backspace አንድላይ በመጫን ቃላቱን ማጥፍት የቻላል፡፡

የ ማውሳችንን ከርሰር (አቅጣጫ አመልካች) ከአንድ ቃል ወደ ቀጣይ ለመውስድ Ctrl እና ወደምንፈልገው እቃጣጫ አይነት የ አቅጣጫን ቁልፍ መጫን፡፡ ምሳሌ Ctrl እና ኪቦርዳችን ላይ የሚገኘውን የቀኝ አቅጣጫ አመልካች ስንጫን ቀጣይ ወዳለው ቃል ያዘልለናል፡፡

Keyboard Shortcuts 

ዴስክቶፓችንን ፎቶ ለማንሳት ከኪቦርዳችን ላይ ከ Function Key (F1,F2,F3…) መጨረሻ ላይ የሚገኘውን PrtSc (Print Screen ) የሚለውን በመጫን ቀጥሎም የተፈለገወቦታ ላይ ፔስት ማድረግ፡፡ ለምሳሌ Paint ን በመክፈት በቅድሚያ PrtSc በመጫን ቀጥሎም Paint ላይ ፔስት በመድረግ የዴስክቶፓችን ፎቶ ሴቭ ማድረግ እንችላላን፡፡ ፎቶ ማንሳት የፈለግነው አክቲቭ የሆነውን መስኮት ብቻ ከሆነ Alt እና PrtSc በመጫን ማንሳት ይቻልል፡፡

ተጨማሪ አቋራጮች 

  • Alt እና F4 አክቲቭ የሆነውን መስኮት ለመዝጋት 
  • Alt እነ W አክቲቭ የሀነውን የብራውሰር ታብ ለመዝጋት 
  • Start እና D ሁሉንም መስኮቶች ወደታች ታስክ ባር ላይ ለማውረድ 
  •  Ctrl እና Shift እና Esc ታስክ ማናጀር ለማስጀመር 
  • Start እና Pause/Break የኮምውተራችንን ጠቅላለ መረጃ ለማኘት 
  • የዌብሳይት አድራሻ ስንፅፍ መጀመሪያ ላይ www መጨረሻ ላይ .com ላመስገባት የምንፈልገውን አድራሻ ከፃፍን በኋላ Ctrl እና Enter መጫን፡፡ መጨረሻ ላይ .net ከፈለግን ደግሞCtrl፤Shift እና Enter መጫን፡፡ 
  • ብራወውሰራችን ላይ የተዘጋን ታብ በድጋ ለመክፈተ Ctrl ፤ Shift እና T መጫን 
  • የፋይል ስም ለመቀየር ፋይልን ከመረጥን በኋላ F2 መጫን
  •  ኮምፒውተራችን ለመቆለፍ Start እና L

0 comments:

Post a Comment

ShareThis