ኤድዋርድ ስኖውደን ማን ነው ?


ኤድዋርድ ስኖውደን አሜሪካዊ የኮምፒውተር ባለሙያ፣ ዩቁድሞ የ ሲ.አይ..ኤ እና ኤን.ኤስ.ኤ ሰራተኛ የነበረ ከ $200,000 በላይ ተከፋይ የነበረ የአሜሪካን መንግስት ሚስጥር ለህዝብ ይፋ የደረገ የ30 አመት ወጣት ነው፡፡ ይፋ የወጡት በተለይ የ አን.እስ.ኤ. የጅምላ ስለላ ፐረግራም ከ እስራኤል ፤ካናዳ፤ብሪተይን እና ኖረዋይን የስለላ ድርጅቶች ድጋፍ ሲያገኝ እንደነበር ይፋ አድርጓል፡፡ ስኖወድን ይፋ ያደርገው ሚስጥር በአሜሪካ ታሪክ ከፍተኛው ነወ ተብሏል፡፡ በ አምሪካው ዘ ዋሺንግተን ፖስት እና በ ኢንግሊዙ ዘ ጋርዲያን ጋዜጦች የታተሙት ሚስጥረች ኤን.ኤስ.ኤ. በተለያየ ፐሮጀክቶች የተከፋፈል የጅምላ ስለላ ሲያካሂድ እንደነብር ግልፅ ሆኗል፡፡ ፐሪስም፤ኤክስ ኪይስኮር ፤ቴምፖራ በተባሉት ፕግራሞች በ ሚሊየን የሚቆጠሩ በመላው አለም የሚገኙ የ ስልክ ምስመሮችን ፣ የአጭር መልእክት ፅሁፎችን ፤ እንዲሁም የኢነተርኔት መርብ መረጃ ልውውጦችን ከበስተጀርባ ሆኖ ሳንሱር ሲያደርግ አንደነበር ተጋልጧል፡፡ ስኖውደን በዚህ ድርጊቱም ጀግና፤ አሸባሪ፤ ከሀዲ፤ እንዲሁመ ሀገር ወዳድ ቢባልም እሱ ግን ይህን መረጃ ይፋ ያደረኩት ጀግና ለመባል ወይም የተለየ ስብእና ለመጎናፀፍ ሳይሆን መንግስታችን በኛ ስም እኛ ላይ እያደረገ ያለውን ኢፍትሃዊ ድርጊት ለማገልጥ ብቻ እንደሆን ለ ጋዲያን ጋዜጣ ተናግሯል፡፡ 
 
በ ሰኔ 1983 እ.ኤ.አ. የተወለድው እድዋርድ ጆሴፍ ስኖውደን ለ እን.ኤስ.ኤ በ ቡዝ አለን በተባለ ድርጅት በኮንትራት ሲያገልግል ነበር፡፡ ስኖውደን የ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በማቁዋረጥ የ ኮምፒውተር ትምህርት ከ 1999-2001 እንደገና ከ 2004-2005 ተከታትሎዋል፡፡ በዚህ መሃልም ለውትደርና አመልክቶ ተጣባቂ በመሆን ለ አራት ወራት ስልጠና ውስዶ የነበረ ሲሆን ነግር ግን ብሰልጠናው ወቅት ድንገተኛ የእግር ስብራት ስላጋጠመው ስልጠናውን ሳይጨርስ አቋርጦ ተሰናብቷል፡፡ ከሁለት አመት በኋላም ስኖውደን የመጀመሪያ ስራውን ለ ሲ.አይ.ኤ. በ ጄኔቫ ሲውዘርላንድ ነበር የጀመረው፡፡ ቀጥሎም በ 2009 ሲ.አይ.ኤ. ን በመልቀቅ ለ ዴል እና ቡዝ አለን ለተባሉ የቴክኖሎጂ እና ደህንነት አማካሪ ድርጅቶች አገልግሏል፡፡ ከ ቡዝ አለን ጋር በመሆን ጃፓን ለሚገኘው የ ኤን.ኤስ.ኤ. ቢሮ በኮንትራት ሲያገለግል እዛም ባሳለፋው ጊዜ የ ጃፓንን ባህል እና ቋንቋ መማር ችሏል፡፡ ከጃፓን ቆይታ መልስ ሰኖውደን ቀጥታ ወደ ሃዋኢ የሚገኘው የ ኤን.ኤስ.ኤ. መስሪያ ቤት የታዘወረ ሲሆን በቆይታውም ለመጀመሪያ ጊዜ ኤን.ኤስ.ኤ. በ ራሱ ዜጎች ላይ ፕሪስም በተባል ፕሮጀክት ስም ስልክ በመጥለፍ፤ ኢነተርኔትን ሳነሱር በማድረግ ኢፍትሀዊ እና የግለሰቦችን ነፃነት በሚፃረር መልኩ እነደሚሰራ ተገነዘበ፡፡ 

ስኖውደን ከሚከፈልው $200,000 አመታዊ ደሞዝ እና የተነደላቀቀ ኑሮን ችላ በማለት በግንቦት 2013 ታላላቅ ሚስጥር የያዙ ዶክመንቶችን ኮፒ ማድረግ እንደ ጀመረ ይገመታል፡፡ የሰበሰባቸውን መረጃ ካጠናከረ በኋላ ለ ከለቃው በቅርቡ ህክምና ለተደረገለት የ ሚጥል በሽታ ተጨማሪ ምርምራ ለማድረግ ፍቃድ ተሰጠው፡፡ ለ ሴት ጉዋደኛውም ላልተገለፀ ምክኒያት ለሳምንታት ከ ሀዋኢ እንደሚለቅ ነግሯት ግንቦት 20 2013 ዋደ ሆንግ ኮንግ በረረ፡፡በዚህም ሰሞን የመጀመሪያዉን ሚስጥር በ ጋርዲያን ጋዜጣ አማካኝነት ለህዝብ ይፋ ተደረገ፡፡ በጥቅምት 2013 ሰኖውደን ያወጣቸው መረጃዎች የአለም መነጋገሪያ ሆኑ በተልይ አሜሪካ አጋሮቼ ናቸው ብላ በምትጠራቸው ሀገሮች እንደነ ፈረንሳይ ፤ጀርመን፤ ብሪቴይን፤ሰፔይን፤ብራዚል፤ሜክሲኮ እንዲሁም በመላው አለም ከ 35 ያላነሱ የሀገር ረእሰ ብሀሮችን ግል ስልክ በመጥለፍ ሲሰልሉ እንደ ነበር ይፋ ተደርጓል፡፡

በህዳር 2013 ጋርዲያን ጠቅላላ ኮፒ ከተደረጉት መረጃዎች 1% ብቻ ለህትመት እንዲበቃ መደረጉን ገልጸዋል፡፡ እድዋርድ ስኖውድነ የጀርመኑን የ Whistleblower Prize እና የ 3000 ዩሩ ሽልማት ነሀሴ 2013 ባለተገኘበት ተበርክቶለታል፡፡ በቀድሞ የአሜሪካ ስለላ ሰራተኞች የተቋቋመው የ Sam Adams Award ሽልማትንም በ ጥቅምት 2013 በ ሞስኮ በአካል በመገኘት ተቀብሏል፡፡ በሆንግ ኮንግ ቆይታው ላይ የሚያጠነጥን Verax የተባለ አጭር ፊልም በሆንግ ኮንግ የተሰራ ሲሆን በልብአንጠልጣይ ዘውግ Classified: The Edward Snowden Story የተባለ በ ኤድዋርድ ጆሴፍ ስኖውደን ገድል ላይ ያተኮረ ፊልም ደግሞ በ መስከርም 2014 እንደሚለቀቅ ይተበቃል ፊልሙም ሲገባደድ በነፃ ከኢነተርኔተ ላይ ዳውንሎድ እነደሚደረግ ተገልጧል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከብዙ ውጣ ውረዶች እና ከ ዊኪሊክስ በተደረገልት ድጋፍ በራሺያ ሞስኮ ለእንድ አመት የመኖሪያ ጥገኝነት ተፈቅዶለት በኢዚያው ይገኛል፡፡



 

ShareThis